Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው የሱዳን የአጋርነት ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው የሱዳን የአጋርነት ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ።

ተባበሩት መንግስታት ድርጅ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ጀርመን ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የሱዳን አጋርነት ዓለም አቀፍ ስብሰባ በዛሬው እለት ተካሂዷል።

በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው ስብሰባው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኑ ጉቴሬዝ እንዲሁም የአውሮፓ ሀገራት እና የሌሎች ዓለም ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ስብሰባውን አስመልክተው በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክትም፥ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን እንዲሁም በሱዳን የአጋርነት ስብሰባ ላይ የታደሙትን ሁሉ፣ ለሱዳን የሚያስፈልገውን የፖለቲካ እና የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የኢንተርኔት መድረክ ስላዘጋጁ አመሰግናቸዋለሁ” ብለዋል።

“ይህ ለሱዳን የሽግግር ወቅት በመሆኑ፣ ከእነርሱ ጋር በአንድነት እንቆማለን” ሲሉም አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል።

“ይህች ታላቅ ሀገር እና ሕዝቧ በሙሉ ኃይላቸው ወደ ዕድገት ጎዳና ሲገሠግሱ፣ የልማት አጋሮቻችን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በመልእክታቸው።

“የተ.መ.ድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስንም ለድጋፋቸው አመሰግናቸዋለን” ያሉት ሲሆን፥  “የተ.መ.ድ አባል ሀገራት ድጋፋቸውን ለሱዳን ይለግሱ ዘንድ እንዲያነሣሡ እጋብዛቸዋለሁ” ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.