Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ተጀመረ፡፡

የክልሉ የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር፣ የክልሉና የዞኖች የሴቶች ህፃናትና ወጣች አደረጃጀት የበጎ ፍቃደኞና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ፊልስን አብዱላሂ በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራ የሴቶችና የህፃናትን ጥቃት እንዲሁም የኮሮና ቫይረስን በመከላከል በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በዚህ አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በክረምት 5 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል አረንጓዴ አሻራን ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ሴቶችና ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ስራ ህብረተሰቡን በማስተባበር የበጎ ፈቃደኝነት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክልሉ ሴቶች ህፃናት ናወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ አስናቁ ድረስ በኩላቸው በዚህ አመት በክልሉ ከሚገኙት 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ወጣቶችና ሴቶች 4 ነጥብ 3 ሚሊየን በጎ ፈቃደኛ ሴቶችና ወጣቶችን በተለያዩ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልገሎት ስራ ለማሳተፍ ታቅዶ ወደስራ መገባቱን ገለፀዋል፡፡

በጎ ፈቃደኛ ሴቶችና ወጣቶች በክረምት በሚሰሩት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መንግስት ለስራ የሚያወጣውን 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ለማዳን መታቀዱንም ጠቁመዋል፡፡

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.