Fana: At a Speed of Life!

ዋተር ኤድ፣ ሴቭ ዘ ቺልድረን እና ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አደገሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዋተር ኤድ፣ ሴቭ ዘ ቺልድረን እና ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አደገሩ ፡፡

ፕሮጀክቱ በቪዲዮ ኮንፍረንስ በይፋ በተጀመረበት ወቅት የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የጤና ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች ተሳትፍዋል ፡፡

ፕሮጀክቱ የንፅህና ቁሳቁሶችን የሚያቀርብ ሲሆን፥ ማህበረሰቡን ተላላፊ ከሆኑ በሽታዎች በዘላቂነት ለመከላከል ይረዳል ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም የንፅህና አጠባበቅ ልምድን መለወጥ እና ወሳኝ በሆኑ አካባቢዎች የንፅህና አጠባበቅ ተቋማት መክፈት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በእንግሊዝ አለም አቀፍ ልማት ድርጅት የሚደገፈው ፕሮጀክቱ በንጽህና አጠባበቅ ልምድ መልዕክቶችን ለ10 ሚሊየን ለሚቆጠሩ ሰዎች ያደርሳል ተብሏል፡፡

እንዲሁም የእጅ መታጠቢያዎችን በጤና ጣቢያዎች ፣ በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ወሳኝ የህዝብ ቦታዎች ላይ ለመትከል አቅዷል፡፡

በተጨማሪም የማቆያ ቦታዎች እና የጤና ማእከሎች ንፅህናን ለመጠበቅ የሚያገለግሉ እንደ የአልኮል ያሉ የንህፅና መጠበቂያዎችን ይሰጣል ፡፡

ይህም በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ይተገበራል ነው የተባለው።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.