Fana: At a Speed of Life!

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች ከ11 እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በ25 እና በ በ11 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት ተቀጡ፡፡

የ64 ዓመቱ ተከሳሽ ነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዕድሜያቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆኑ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞባቸዋል፡፡

በዚህም ተከሳሹ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዐቃቂ ቃሊቲ ምድብ ፅህፈት ቤት የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን መስርቶበታል፡፡

ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ ማስረጃ አቅርቦ በማሰማቱ እንዲሁም ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ ብሎታል፡፡

በዚህም ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ60 አመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የ15 ዓመት የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከ9 ወር ጽኑ ተቀጥቷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቁጥራቸው እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲያገኝም በፍጥነት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ መገለፁን ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.