Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከአፍሪካ የመነጨ መፍትሔን ማበጀት ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከአፍሪካ የመነጨ መፍትሔን ማበጀት ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ውይይቱ ውጤታማ እንደነበርም ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ይህን አህጉራዊ ጠቀሜታ ያለው የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላስተባበሩት የአፍሪካ ህብረት ሰብሳቢ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ እና ለህብረቱ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፅሁፋቸው የፓን አፍሪካዊነት መንፈስ ያለው አህጉራዊ ተቋማችን ለአፍሪካ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን ውይይቶች ለማካሄድ ትክክለኛው ሥፍራ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

በተጨማሪም ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና የጋራ ብልጽግና የሚያገኙበትን ዕድል ይዟል ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.