Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ውይይቱን አስመልክቱ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በልማት ፕሮጀክቶች፣ በኢትዮጵያና በፈረንሳይ ግንኙነት እንዲሁም ኮቪድ19ን ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ተወያይተናል” ብለዋል።

ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ የምታደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.