Fana: At a Speed of Life!

የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ ለህዝብ ውይይት ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ኮሚሽን አስተባባሪት እየተዘጋጀ ያለው የሀገሪቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ የመነሻ ሰነድ ለህዝብ ውይይት ሊቀርብ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ።

በመሪ እቅዱ ላይ የሚካሄደው የህዝብ የውይይት መድረክም ከፊታችን ሰኞ ሰኔ 22 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ11 ቀናት የሚካሄድ መሆኑንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።

የህዝብ የውይይት መድረክ ዋነኛ ዓላማም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በዕድቅ ዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፉ ማስቻል፣ የተለያዩ የጥናት ውጤቶችን በዋና ግብአትነት የወሰደውን እቅዱን መነሻ ሰነድ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተሰበሰበ ግብአት ማዳበርና ከባለድርሻ አካላት የሚነሱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠት መሆኑንም አስታውቋል።

በተያዘው መርሃ ግብር መሰረትም ሰኞ ሰኔ 22 2012 ዓ.ም የፕላንና ልማት ኮሚሽን፣ ሰኔ 23 የግብርና ዘርፍ፣ ሰኔ 24 የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ፣ ሰኔ 25 የቱሪዝም ልማት ዘርፍ፣ ሰኔ 26 የማዕድን ሀብት ልማት ዘፍር፣ ሰኔ 29 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ የመሰረተ ልማት እና የውሃ መስኖና ኢነርጂ ዘርፍ፣ ሰኔ 30 የልማት ፋይናንስ፣ ሐምሌ 3 የፍትህና መልካም አስተዳደር እንዲሁም ሐምሌ 4 የልማት፣ ሰላምና አካታችነት ዘርፎች የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ ላይ በኃላፊዎች አማካኝነት ለውይይት የሚቀርብ መሆኑም ታውቋል።

የውይይት መድረኮቹም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ የሚተላለፉ መሆኑንም ለማሳወቅ እንወዳለን።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.