Fana: At a Speed of Life!

በ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ ላይ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ኮሚሽን አስተባባሪት እየተዘጋጀ ባለው የሀገሪቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ የመነሻ ሰነድ ላይ ህዝባዊ ውይይት መካሄድ ጀምሯል።

በመሪ እቅዱ ላይ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ውይይት መድረክ ዛሬን ጨምሮ ለ11 ቀናት የሚካሄድ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የውይይት መድረኩ ባለድርሻ አካላት በዕድቅ ዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፉ ማስቻል፣ የተለያዩ የጥናት ውጤቶችን በዋና ግብአትነት የወሰደውን እቅዱን መነሻ ሰነድ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተሰበሰበ ግብአት ማዳበርና ከባለድርሻ አካላት የሚነሱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠትን አላማው ያደረገው ነው ተብሏል።

በዛሬው እለትም የፕላንና ልማት ኮሚሽን የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ ላይ በኃላፊዎች ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።

ከዚህ ባለፈም ነገ ሰኔ 23 ቀን የግብርና ዘርፍ፣ ሰኔ 24 የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ፣ ሰኔ 25 የቱሪዝም ልማት ዘርፍ፣ ሰኔ 26 የማዕድን ሀብት ልማት ዘፍር፣ ሰኔ 29 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ የመሰረተ ልማት እና የውሃ መስኖና ኢነርጂ ዘርፍ፣ ሰኔ 30 የልማት ፋይናንስ፣ ሐምሌ 3 የፍትህና መልካም አስተዳደር እንዲሁም ሐምሌ 4 የልማት፣ ሰላምና አካታችነት ዘርፎች የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል።

የውይይት መድረኮቹ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.