Fana: At a Speed of Life!

የኩፍኝ በሽታ የክትባት ዘመቻ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የኩፍኝ በሽታ የክትባት ዘመቻ ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡

ቢሮው ዘመቻውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ እድሜያቸው ከ9 ወር እስከ 5 አመት ለሆናቸው ህፃናት ከሰኔ 23 ቀን እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ክትባቱ ይሰጣል ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ክትባቱ በተጠቀሱት ቀናት በሁሉም ጤና ተቋማት እና ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

በክትባቱ ወቅት ህፃናት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ወላጆች ወይም አሳዳጊዎችም ልጆቻቸውን በማስከተብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.