Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ለአዲሱ የማላዊ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአዲሱ የማላዊ ፕሬዚዳንት ዶክተር ላዛረስ ቻክዌራን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽ እንዲሁም በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ አብረው እንደሚሰሩ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የማላዊ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ላዛሩስ ቻክዌራ በሃገሪቱ እንደገና በተካሄደው ፕሬዚንደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎት ናንት ቃለ መሃላ መፈጸማቸው ይታወሳል።

ላዛሩስ በምርጫው 58 ነጥብ 57 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሁን በሥልጣን ላይ ያሉትን ተፎካካሪያቸውን ፒተር ሙታሪካን ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በተካሄደው ምርጫ እንዳሸነፉ መገለጹም አይዘነጋም።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.