Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ራሳቸውን አይነኬ ነን በማለት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በሚጥሩ ቡድኖች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል- አቶ ንጉሱ ጥላሁን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት ራሳቸውን አይነኬ ነን በማለት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በሚጥሩ ቡድኖች ላይ እርምጃ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደረናገሩት፥ መንግስት ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ነገሮችን አይቶ እንዳላየ ቢያልፍም ትዕግስቱ ድክመት የመሰላቸው አኩራፊ ቡድኖች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና በህዝቦች ደህንነት ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀምረዋል።

በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የመንግስትን የትዕግስት ገደብ አልፈዋል ያሉት አቶ ንጉሱ፥ “እኛ የበላይ እንሁን፣ እኛ አድራጊ ፈጣሪ ካልሆን ሀገር ትፍረስ የሚሉ አካላትን መታገሱ አብቅቷል” ብለዋል።

መንግስት ከዚህ በኋላ ህግ በማስከበር የትኛውንም አካል ከመጠየቅ ወደ ኋላ እንደማይልም አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።

መንግስት ከየትኛውም ቡድን ይሁኑ ሀገር ለማፈራረስ ተልዕኮ የሚቀበሉ ግለሶቦችና ቡድኖችንም ሆነ ተልዕኮ ሰጭዎችን በህግ ተጠያቂ ያደርጋልም ብለዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.