Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የነበረው የፀጥታ ችግር በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ቁጥጥር ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ቀናት በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ቁጥጥር ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደሩን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።

ይህንን ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋት ከፍተኛ እድል የፈጠረውን አጋጣሚ መነሻ በማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የቢሮ ሃላፊው ዶክተር መንግስቱ በቀለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በሁኔታው ይበልጥ ተጋላጭ ለነበሩ አካባቢዎች ትኩረት በመስጠትም የመለየትና የቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡም ከምን ጊዜውም በበለጠ የቫይረሱን ስርጭት መገደብ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲንቀሳቀስ ጠይቀዋል።

በቫይረሱ የመያዝ አጠራጣሪ ምልክቶችን በሚያይበት አጋጣሚም ራስን በቤት አካባቢ በመወሰን የጤና ባለሞያ እገዛን መጠየቅ ይገባዋል ነው ያሉት።

በለይቶ ማቆያዎች አካባቢ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ መቀዛቀዝን ያነሱት የቢሮ ሃላፊው፥ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

መጪው ጊዜ የቫይረሱ ስርጭት ይበልጥ ይጨምራል ተብሎ የሚጠበቅበት በመሆኑም በርካታ የበጎ ፍቃድ ወጣቶች፤ ባለሞያዎችና መምህራን ስራውን እንዲያግዙ ጠይቀዋል።

በትእግስት ስለሺ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.