Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና ኮሪያ ኤግዚም ባንክ መካከል የ70 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ከኮሪያ ኤግዚም ባንክ ጋር የ70 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረመች።

ከብድሩ ውስጥ 40 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላሩ ኢትዮጵያ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት ላወጣችው እቅድ ማስፈፀሚያ የበጀት ጉድለት እንዳይገጥማት ይውላል ተብሏል።

ቀሪው 30 ሚሊየን ዶላር ደግሞ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለሚያግዙ የህክምና ቁሳቁሶች ግዥ እና የጤና ስርዓቱን ለማሻሻል እንዲሁም ለአቅም ግንባታ ስራዎች እንደሚውል ተገልጿል።

የብድር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የኮሪያ ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ባንግ ሙንዩ በቪዲዮ በታገዘ ስነ ስርአት ተፈራርመዋል።

ከባንኩ ጋር የተፈረመው የ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የብድር ስምምነት በረጅም ጊዜ የሚከፈል ነው መባሉንም የገንዘብ ሚኒስቴር ያደረሰን መረጃ ያሳያል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.