Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በአለም አቀፍ ደረጃ በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ዙሪያ ከአሜሪካ እና ሩሲያ ጋር የመደራደር ፍላጎት እንደሌላት ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)   ቻይና በአለም አቀፍ ደረጃ በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ዙሪያ ከአሜሪካ እና ሩሲያ ጋር የመደራደር ፍላጎት እንደሌላት አስታወቀች።

አሜሪካ እና ሩሲያ በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ላይ ለመነጋገር መስማማታቸውን ተከትሎ የቻይና አቋም ሲጠበቅ ነበር።

የቻይና የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ዳይሬክተር ፉ ኮንግ ፤ የጦር አቅምን መገደብ ላይ የሚደረግ ድርድር ቤጂንግ ልትቆምርበት የማትፈልግው ጉዳይ ነው ብለዋል።

አሜሪካ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ የምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደሚያሰጋት የገለጸችው ቻይና የጦር አቅሟን ከመገደብ ይልቅ የማጠናከር እቅድ እንዳላት አስታወቃለች።

በቻይና አቅራቢያ በሚገኙ የጦር ሰፈሮች የአሜሪካ የረዥም እና መካከለኛ ርቀት ሚሳኤሎችን  የቀጣናው ስጋት መሆናቸውንም ገልጻለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.