Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ስም የተለያዩ የመታሰቢያ ቦታዎች ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ስም የተለያዩ የመታሰቢያ ቦታዎች ተሰየሙ።

ለድምፃዊው መታሰቢያዎቹ የተሰየሙለት በአቃቂ ክፍለ ከተማ ገላን አካባቢ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ጀሞ የሚወስደው መንገድ፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ድልድይና በሂልተን ሆቴል አካባቢ ያለው ፓርክ ናቸው።

በስሙም የመታሰቢያ ሐውልት በከተማዋ ለማቆም በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አካባቢ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ለአርቲስቱ መታሰቢያዎቹ የተሰየሙት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትብብር እንደሆነ ተገልጿል።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ”በሐጫሉ ስም የተሰየሙት ትምህርት ቤት፣ መንገድ፣ ድልድይና ፓርክ እውነተኛ ማንነቱን ላይገልጹ ይችላሉ ብለዋል።

አያይዘውም እውነተኛው ሐጫሉ ለዘላለም በልባችን ይኖራልም ነው ያሉት።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው ”ሐጫሉ ዕድሜ ዘመኑን በሁሉም መስክ ሲታገል የኖረ ጀግና ነው” ብለዋል።

በተሸረበበት ሴራ ሐጫሉ ቢሞትም፤ ሴራዎችን በማክሸፍ የታገለለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ሁሉም በጋራ እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.