Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ27 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ27 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላይ በሃገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ821 ሺህ በልጧል ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም በሃገሪቱ ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡

ህንድ ከዚህ በፊት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ያላላች ሲሆን አሁን ቫይረሱ በፍጥነት በመዛመቱ ምክንያት እንደገና እገዳ አስቀምጣለች፡፡

የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም ቫይረሱ መስፋፋቱን ተከትሎ ከጤና ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ምክክር ቫይረሱ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች እንደገና የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ፈቅደዋል፡፡

በሌላ በኩል በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ12 ሚሊየን አልፏል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.