Fana: At a Speed of Life!

ችግኝ የሚተከልባቸው ቦታዎች ኃላፊነት የሚወስድ አካል እንዲኖራቸው መደረጉ ተገለፀ 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሁኑ ወቅት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ችግኝ የሚተከልባቸው ቦታዎች ኃላፊነት የሚወስድ አካል ኖሯቸው እየተተገበረ መሆኑን የአካባቢ ደን እና  አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ ተናገሩ።

ኮሚሽነሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እየተተከሉ ካሉ ችግኞች አብዛኛውን ድርሻ የሚይዙት ምጣኔ ሀብታዊ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውን  አብራርተዋል።

ቅድሚያ የኮሮና ቫይረስ መከላከያዎችን በመተግበር ችግኝ የመትከል መርሃ ግብሩ በእቅዱ መሰረት እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ኮሚሽነሩ ባለፈው ዓመት ከተተከሉ ችግኞች በተደረገ ጥናት ከ82 በመቶ በላይ ጸድቋል ያሉ ሲሆን፥ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ደግሞ ለየት ያለ አካሄድም እየተከተለ ይገኛል።

አዲሱ አካሄድ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ከተተከሉ በኋላ የሚስተዋሉ አንክብካቤ ክፍተቶችን ይሸፍናል በሚል እምነት ተጥሎታታል።

አብዛኛዎች ችግኞች በሚተከሉበት አካቢቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉ፤ ምጣኔ ሀብታዊ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ ነው ብለዋል።

በስላባት ማናዬ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.