Fana: At a Speed of Life!

በዶሃ ፎረም የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ከየአል ሱሌይቲን ግሩፕ ሊቀ መንበር ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ19ኛው የዶሃ ፎረም ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ከየአል ሱሌይቲን ግሩፕ ሊቀ መንበር ጋር ተወያየ።

ልዑኩ ከአል ሱሌይቲን ግሩፕ ሊቀ መንበር ሼክ አብደላህ ሳሌም አል ሱሌይቲን ጋር ቆይታ አድርጓል።

በፕሮግራሙ ላይ የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ፣ በዶሃ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ እና የሚሲዮኑ ዲፕሎማቶች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እና ሌሎች የልዑክ ቡድን አባላት ተሳትፈዋል።

ሊቀ መንበሩ በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በመደገፍ፣ እንዲሁም በየዓመቱ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ቀን ስፖንሰር በማድረግ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

አል ሱሌይቲን ግሩፕ በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ መዋዕለ ንዋዩን ለማፍሰስ መሬት እንደተረከበና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚሸጋገርም ሊቀ መንበሩ ተናግረዋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ለሚያደርገው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መገለጹን በዶካ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.