Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ጓጉሳ ሽጉዳድ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓጉሳ ሽጉዳድ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አማረ ፈረደ ለአብመድ እንደተናገሩት፥ አደጋው ዛሬ ረፋድ 3 ሰዓት ላይ አዲስ ዓለም በምትባል የገጠር ከተማ አካባቢ የደረሰ ነው።

አደጋው ከጅጋ ወደ ባሕር ዳር ይጓዝ የነበረ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ፥ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ የደረሰ ሲሆን የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ ከባድ እና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአቅራቢያው ወደ ሚገኙ የጤና ተቋማት ተልከዋልም ነው ያሉት።

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፥ የሟቾችን አድራሻ የመለየት ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በተያዘው ዓመት እየደረሱ ያሉ የትራፊክ አደጋዎችና እያደረሱ ያለው የጉዳት መጠን በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.