Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በኢትዮጵያ አሳሰቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በኢትዮጵያ አሳሰቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አስታውቋል።

የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት ትናንት ምሽት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዜና መጽሄት በነበራቸው ቆይታ፥  በወጣቶች ዘንድ በመዝናኛ ቦታዎችና በተለያዩ እንቅሰቃሴዎች ላይ ቸልተኝነት እንደሚስተዋልባቸው ገልፀዋል።

ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችም ቢሆኑ የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል ረገድ ጥንቃቄዎቹ ከፍተኛ መዘናጋት የሚታይበት መሆኑ ነው የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ የገለፁት።

ይሄ መዘናጋት ከፍተኛ ዋጋ እንዳያስከፍል ቦርዱ መንግስት የማስተካከያ እርምጃዎችን እንዲወስድ ምክረ ሀሳብ ማቅረቡንም አንስተዋል።

አሁን ላይ መንግስት የሚሰጠውንም ትምህርት አጠናክሮ የሚቀጥልበት ህጋዊ እርምጃዎችንም ወደ መውሰድ የሚገባበት ጊዜ መድረሱንም ተናግረዋል።

ቦርዱ በሪፖርት፣ በመስክ ምልክታና በተለያዩ መንገዶች የአስፈፃሚውን አካል ቁጥጥር እያደረግ መሆኑ አንስተዋል አቶ ጴጥሮስ።

ኮሮና ቫይረስ የእያንዳንዱ ሰው ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ከምንም ጊዜ በላይ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ሲሉ ቫይረሱን የመከላከያ መንገዶችን ገቢራዊ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.