Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 6፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ስታዲየም በነገው ዕለት ይጀመራል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአጭር፣ በመካከለኛ ርቀት፣ በ3 ሺህ ሜ.መሰናክል፣ በእርምጃና በሜዳ ተግባራት ከታህሳስ 7 እስከ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበበ ስታዲየም ነው የሚካሄደው፡፡

በመክፈቻው እለትም የአሎሎ ውርወራ ማጣሪያና ፍፃሜ፣ የስሉስ ዝላይ ማጣሪያና ፍፃሜ፣ እንዲሁም ከ100 ሜትር እስከ 800 ሜትር የማጣሪያ ውድድሮች እንደሚካሄዱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.