Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 328 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6ሺህ 911 የላቦራቶሪ ምርመራ ሰዎች 328 የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 8 ሺህ 803 ደርሷል።

የጤና ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ባለፉት 24 ሰዓት በአስክሬን ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ 2 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 150 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 250፣ ከጋምቤላ ክልል 27፣ ከኦሮሚያ ክልል 15፣ ከትግራይ ክልል 13፣ ከአፋር ክልል 8፣ ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር 5፣ ከሱማሌ ክልል 5፣ ከሲዳማ ክልል 3፣ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል 1፣ እና ከአማራ ክልል 1 ናቸው ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት ተጨማሪ 46 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 814 መድረሱ ታውቋል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 3 ሺህ 837 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 37 በፀና የታመሙ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 309 ሺህ 639 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.