Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የባህል ቡድን አስመራ ገብቷል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ60 በላይ አባላትን የያዘው የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ኤርትራ ገብቷል።

አስመራ ሲገባም የኤርትራ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውለታል።

ልዑኩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ቲያትር፣ ከታዋቂ ደምጻውያንና የጃኖ ባንድ ሙዚቀኞችን ያካተተና ከ60 በላይ አባላትን የያዘ ነው።

የባህል በድኑ ጉዞ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የተፈጠረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው።

ቡድኑ ለአንድ ሳምንት በኤርትራ የሚቆይ መሆኑም ታውቋል።

የባህል ቡድኑ በኤርትራ ቆይታው አስመራን ጨምሮ በከረን እና ምፅዋ ከተሞች የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

የኤርትራ የባህል ቡድን ባሳለፍነው አመት የካቲት ወር ላይ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በባህርዳር እና በሀዋሳ ከተሞች ዝግጅቶችን ማቅረቡ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.