Fana: At a Speed of Life!

ተመድ የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የ10 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር የድጋፍ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የ10 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር የድጋፍ ጥሪ አቀረበ፡፡

ድርጅቱ ቫይረሱን ለመዋጋት ለማሰባሰብ የጠየቀው የገንዘብ መጠን ከእስካሁኑ ትልቁ ነው ተብሏል፡፡

ገንዘቡ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሀገራት ጥቅም ላይ ይውላል ነው የተባለው፡፡

በሌላ በኩል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ እስከ 256 ሚሊየን ሰዎች ረሃብ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.