Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በቻይና የኮሚዩኒስት ፓርቲ አባላት ላይ የጉዞ እገዳ ልትጥል ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በቻይና የኮሚዩኒስት ፓርቲ አባላት ላይ የጉዞ እገዳ ለመጣል እያሰበ መሆኑ ተሰማ።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ምንጮች ዋቢ ያደረገው የሬውተርስ ዘገባ እቅዱ በረቂቅ ደረጃ መዘጋጀቱን ያስረዳል፡፡

እቅዱ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ቀርቦ የሚጸድቅ ከሆነ አሜሪካ በቻይና ላይ ከወሰደቻቸው እርምጃዎች ጠንካራው ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡

በእቅዱ መሰረት ከኮሚዩኒስት ፓርቲ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተጨማሪ ለቻይና በወገነ መልኩ በአሜሪካ ጥቅም ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦችና የንግድ ድርጅቶችም የእገዳው ሰለባ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

የአሁኑ የአሜሪካ እርምጃ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ፍጥጫ ወደባሰ መካረር ያስገባዋልም ነው የተባለው።

ሊጣል ይችላል የተባለው እገዳ በሚሊየኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የሚተገበር መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

አሜሪካ እገዳውን ካጸደቀች የቻይና መንግስትም ወደ ሃገሪቱ በሚገቡ አሜሪካውያን ላይ አፀፋ ሊወስድ እንደሚችልም ዘገባው ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.