Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 344 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ7 ሺህ 407 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 344 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ 13 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አራቱ የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው የቆዩ እንዲሁም ዘጠኙ ከአስከሬን ላይ በተደረገ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ናቸው፡፡

አሁን ላይም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 163 መድረሱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 9 ሺህ 147 ደርሷል፡፡

በትናንትናው እለት 86 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 900 ሆኗል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.