Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ዜጎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ አላስገድድም አሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮና ቫይረስን መስፋፋት ለመግታት በሚል ዜጎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ አላስገድድም አሉ።

የአሜሪካ የተላላፊ በሽታዎች ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ የግዛትና የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ዜጎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ በተቻለ መጠን እንዲያስገድዱ ጠይቀው ነበር፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕም የባለሙያውን ጥያቄ ተከትሎ በሰጡት አስተያየት ጭምብል መጠቀምን እንደ ግዴታ መታየት የለበትም ብለዋል፡፡

አያይዘውም ህዝቡ ነጻነት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል በንግግራቸው፡፡

በአሜሪካ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል የመጠቀም ጉዳይ ፖለቲካዊ አንድምታ ይዟል።

ከቀናት በፊት የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ህዝቡ ጭምብል እንዲጠቀም መጠየቁ ይታወሳል።

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.