Fana: At a Speed of Life!

የመሰረተ ልማት አውታር የሆኑ የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን በመቁረጥ ስያጓጉዙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን ከቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ከወዳደቁ የፕላስቲክ እቃዎች ጋር በማደባለቅ ከገብረ ጉራቻ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ግምቱ በውል ያልታወቀ የኤሌክትሪክ ሽቦን ከሱሉልታ ፍተሻ ኬላ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፌዴራል ፖሊስ የትራፊክ ፍሰት ተቆጣጣሪዎች እና ወንጀል መከላከል አባላት እጅ ከፍንጅ መያዙን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በወንጀል መከላከል ዘርፍ ፀጥታና ህግ ማስከበር ዳይሮክቶሬት ዋና ኢንስፔክተር አብዲሳ ዋቅጅራ እንደገለጹት ÷ ‹‹ የህብረተሰቡን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ኬላው ላይ ይደርሳሉ በተባለበት ሰዓት የተጠናከረ ቁጥጥር በማድረግ የመንግስት ንብረት የሆነውን የኤሌክትሪክ ሽቦ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል››፡፡ የፌዴራል መንገዶች ትራፊክ ቁጥጥርና አደጋ ምርመራ ቡድን መሪ ምክትል ኢንስፔክተር ዳዊት አሰፋ በበኩላቸው ÷ ‹‹ በልማት አውታሮች ላይ የሚፈጸም ዝርፊያ ሀገርንና ህዝብን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ እንዲህ አይነቱን ተግባር የሚፈጽሙ ግለሰቦች ምን ጊዜም ከህግ አስከባሪውም ሆነ ከህብረተሰቡ ሊደበቁ እንደማይችሉና የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ይህ የተጠናከረ የቁጥጥር ተግባር ማሳያ ይሆናል ብለዋል›› ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን ከቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ከወዳደቁ የፕላስቲክ እቃዎች ጋር በማደባለቅ ከገብረ ጉራቻ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ግምቱ በውል ያልታወቀ የኤሌክትሪክ ሽቦን ከሱሉልታ ፍተሻ ኬላ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፌዴራል ፖሊስ የትራፊክ ፍሰት ተቆጣጣሪዎች እና ወንጀል መከላከል አባላት እጅ ከፍንጅ መያዙን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በወንጀል መከላከል ዘርፍ ፀጥታና ህግ ማስከበር ዳይሮክቶሬት ዋና ኢንስፔክተር አብዲሳ ዋቅጅራ እንደገለጹት ÷ ‹‹ የህብረተሰቡን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ኬላው ላይ ይደርሳሉ በተባለበት ሰዓት የተጠናከረ ቁጥጥር በማድረግ የመንግስት ንብረት የሆነውን የኤሌክትሪክ ሽቦ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል››፡፡

የፌዴራል መንገዶች ትራፊክ ቁጥጥርና አደጋ ምርመራ ቡድን መሪ ምክትል ኢንስፔክተር ዳዊት አሰፋ በበኩላቸው ÷ ‹‹ በልማት አውታሮች ላይ የሚፈጸም ዝርፊያ ሀገርንና ህዝብን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ እንዲህ አይነቱን ተግባር የሚፈጽሙ ግለሰቦች ምን ጊዜም ከህግ አስከባሪውም ሆነ ከህብረተሰቡ ሊደበቁ እንደማይችሉና የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ይህ የተጠናከረ የቁጥጥር ተግባር ማሳያ ይሆናል ብለዋል›› ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.