Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ማርስ መንኮራኩር አመጠቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ማርስ መንኮራኩር አመጠቀች።

መንኮራኩሯ 500 ሚሊየን ኪሎ ሜትር የምትጓዝ ሲሆን በፈረንጆቹ 2021 የካቲት ወር ላይ ማርስ ትደርሳለች ተብሏል፡፡

የመንኮራኩሯ መድረሻ ጊዜም ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ምስረታ 50ኛ አመት ጋር ተገጣጥሟል።

ከጃፓኑ ታኔጋሽማ የተነሳችውና “ሆፕ” የተባለችው መንኮራኩር የማርስን የአየር ሁኔታ እና ጠባይ እንደምታጠና ይጠበቃል።

በማርስ ካረፈች በኋላም እስካሁን ስለ ፕላኔቷ ያልታወቁና ያልተደረሰባቸውን መረጃዎች ታደርሳለች ነው የተባለው።

መንኮራኩሯን ባለፈው ሳምንት ሁለት ጊዜ ለማስወንጨፍ ተሞክሮ በአየር ሁኔታ ሳቢያ ሳይሳካ ቀርቶ ነበር።

የአሁኑ የማምጠቅ ሙከራ ነዳጅ ላይ ብቻ ለተመሰረተው የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እውቀት ተኮር ወደሆነ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ለሚደረገው ጥረት ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.