Fana: At a Speed of Life!

በከፊል ዝግ የነበረው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የችሎት ስራ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በከፊል ዝግ የነበረው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የችሎት ስራ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል።

በዚህም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረሰ በሁሉም ፍርድ ቤቶች የመልስ መልስ፣ አስተያየቶች፣ የትዕዛዝ ውጤቶችን ለመቀበል የተቀጠሩ እንዲሁም እልባት ለመስጠት ጥቂት ሂደት የቀራቸው ጉዳዮች እና እስረኛ ያላቸው መዛግብት በየቀጠሮ ቀናቸው የማስተናገድ ስራ ይሰራል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃለ አቀባይ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ነዋይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የሚታዩ ጉዳዮች አስቸኳይነት በዳኛው፣ በፍርድ ቤቱ እንዲሁም በየደረጃው በሚገኝ አመራር አሳማኝነቱ ካልታመነበት ለቀጣዩ አመት የሚቀጠር ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ፍርድ ቤቶቹ አዳዲስ መዝገቦችን ማለትም የቀጥታ ክስ፣ ይግባኝ እና አፈጻጸም መዝገቦችን ደግሞ ከነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ማየት ይጀምራሉ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለጉዳዮች የሚቀርቡ አቤቱታዎች ይስተናገዳሉም ብለዋል፡፡

ከክልል የሚመጡ የሰበር ጉዳዮች ግን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል ተለዋጭ የስራ አቅጣጫ እስከሚሰጥ አይስተናገዱም።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.