Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ “አንድ መምህር ለአንድ ቤተሰብ” በሚል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ “አንድ መምህር ለአንድ ቤተሰብ” በሚል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ከወጣቶች እና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር ጋር በመተባበር ነው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብሩን የጀመረው።

በትናንትናው እለት ይፋ በተደረገው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሰራ ኃላፊዎች፣ የከተማው መምሀራን ማህበር አባላት፣ የአዲስ አበባ የወጣቶችና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር ፣ መምህራን እና ሌሎች ተገኝተውበታል።

የክረምት በጎ ፍቃድ ማጠናከሪያ ትምህርት መርሃ ግብሩ በኮቪድ-19 ወረርሽን ሳቢያ የተቋረጠውን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ለማካካስ እና ተማሪዎች ለ2013 የትምህርት ዘመን ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑ ያግዛል ተብሏል።

በዚህ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሃግብር ከመምህራን በተጨማሪ ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ መምህራን በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ላይ መሆናቸዉ የተገለጸ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ አንበሳዉን ድርሻ እንደሚወስዱ መገለፀጹንም የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.