Fana: At a Speed of Life!

ዚምባብዌ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሰአት እላፊ አወጀች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሰአት እላፊ አወጁ፡፡

ሰአት እላፊው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በማሰብ የታወጀ ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከዛሬ ጀምሮ የታወጀውን ሰአት እላፊ የፀጥታ አካላት እንዲያስተገብሩም ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

መንግስት የሃገሬው ዜጎች ምግብን ጨምሮ የጤና አገልግሎት ለማግኘትና በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች ውጭ ከቤት እንዳይወጡ አሳስቧል፡፡

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ግን ሰአት እላፊው በቀጣዩ ሳምንት መንግስትን በመቃወም ሊያደርጉት ያሰቡትን የተቃውሞ ሰልፍ ለማስቆም የታወጀ ነው በሚል ውሳኔውን ኮንነውታል፡፡

በርካቶች በሃገሪቱ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ሰፍኗል በሚል በፕሬዚዳንት ምናንጋግዋ አስተዳደር ላይ ተቃውሞ እያሰሙ ነው፡፡

በዚምባብዌ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 26ቱ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.