Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በሶሪያ የሚገኙ የቱርክ ወታደሮች ባሉበት እንደሚቆዩ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን በሶሪያ የሚገኙ የቱርክ ወታደሮች ባሉበት እንደሚቆዩ አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ የሶሪያውያን ሰላምና መረጋጋት እስከሚመለስ ድረስ የቱርክ ወታደሮች በሶሪያ ይቆያሉ ብለዋል፡፡

ቱርክ ወታደሮቿን ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ ወደ ሰሜናዊ ሶሪያ ማስገባቷ ይታወሳል፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህም በስፍራው በሚንቀሳቀሱ የአይ ኤስ ቀሪ አባላት እና በሶሪያ የኩርድ ህዝቦች ታጣቂዎች ላይ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ትገኛለች፡፡

ወታደራዊ ዘመቻው በአካባቢው ሰላምን ለማስፈን እና ሶሪያውያን ሰላማዊ ህይወት እንዲጀምሩ ለማድረግ በማሰብ የሚካሄድ መሆኑንም አንካራ በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

ምንጭ፣ ሺንዋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.