Fana: At a Speed of Life!

በናይጄሪያ የነዳጅ ምርቶችን በሚያጓጓዝ መኪና ላይ በደረሰ አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በናይጄሪያ የነዳጅ ምርቶችን ሲያጓጉዝ በነበረ አንድ የጭነት መኪና ላይ በተከሰተ ፍንዳታ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

አደጋው  የተከሰተው በደቡባዊ  ናይጄሪያ የኢዶ እና ዴልታ ግዛቶችን በሚገናኝ አውራ ጎዳና ዋና መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኑም ነው የተነገረው ፡፡

እሳቱ ነዳጅ ከጫነው መኪና  በመንገዱ ላይ  ወደ  ነበሩ ሌሎች ተሽከርካሪዎች በፍጥነት  መሰራጨቱም ተገልጿል።

በወቅቱ በአደጋው አቅራቢያ የነበሩ ብዙ  ሰዎች በእሳት መያያዛቸውን እና ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውን የዓይን እማኞች  ተናግረዋል።

ናይጄሪያ ባላት ደካማ የመንገድ መሰረተ ልማት እንደነዚህ አይነት አደጋዎች በብዛት  መከሰቱ የተለመደ መሆኑም ይገለጻል።

ከሶስት ሳምንት በፊት በሰሜናዊ ቤኒቴ ግዛት በአንድ መንደር አቅራቢያ የነዳጅ ማመላለሻ መኪና  በመፈንዳቱ የ35 ሰዎች ህይወት አልፎ ነበር ፡፡

ከዚያም ባለፈ በአውሮፓውያኑ  በ 2012 በደቡብ-ምዕራብ በፖርት ሃርኮር ከተማ ውስጥ በተመሳሳይ  ሁኔታ   በደረሰው አደጋ ሴቶችን እና ልጆችን ጨምሮ 92 ሰዎችን ህይወት አልፏል ፡፡

ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.