Fana: At a Speed of Life!

በአለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 15 ሚሊየንን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 16፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም አቀፍ ደረጃ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 15 ሚሊየንን ማለፉ ተነግሯል፡፡

እንደጆን ሆፕኪንስ መረጃ በአለም ዙሪያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 15 ነጥብ 2 ሚሊየንን ሲሻገር፥ የ623 ሺህ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

ከአለም በቫይረሱ ክፉኛ እየተጎዳች ያለቸው ሀገር አሜሪካ ስትሆን ከ3 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሲያዙ በትናንትናው እለት የተመዘገበው የ1 ሺህ 33 ሰዎችን ሞት ጨምሮ ቁጥሩ 143 ሺህ 190 መድረሱ ታውቋል፡፡

ብራዚልን ጨምሮ በህንድ እና ደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ ወረርሽኙ እየተስፋፋባቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፦ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.