Fana: At a Speed of Life!

ተመድ የኮሮናቫይረስን ለመዋጋት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 16፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ)የኮሮናቫይረስን ለመዋጋት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ በመሠረታዊነት 132 በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ በድህነት ውስጥ ለሚኖሩ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች የሚውል ድጋፍ ከመሆኑም ባለፈ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ያግዛልም ነው የተባለው

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በየሳምንቱ ወደ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን አዳዲስ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ በሚያዙበት በዚህ ወቅት በወር ከ199 ቢሊዮን ዶላር እስከ 465 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ድጋፍ ያስፈልጋልም ነው ያለው።

ይህ ድጋፍ ምናልባትም ከ9 ወር እስከ አንድ አመት ሊቀጥል እንደሚችል ነው ድርጅቱ ያስታወቀው፡፡

ከዚያም ባለፈ ቀድሞውኑ በፖለቲካ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚፈተኑት በማደግ ላይ ባሉ አገራት የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ወረርሽኙን ለመግታት የተጣሉት ማዕቀቦችን ተከትሎ የመጣው ችግር ይበልጡኑ ፈታኝ ሆኖባቸዋልም ነው ያለው ተመድ ፡፡

የዓለም አቀፉ የሰራተኛ ድርጅት ÷ በታዳጊ ሀገራት ውስጥ ከሚኖሩ አስር ሠራተኞች ውስጥ ሰባት የሚሆኑት ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ ውስጥ ይኖራሉ ብሏል፡፡
ከነዚህ መካከል ብዙዎቹ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ፣ ደሞዝ የማይከፈላቸው እና ያልተከፈላቸው የእንክብካቤ ሠራተኞች እንዲሁም ስደተኞች ናቸው ብሏል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.