Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለ2012 ዓ.ም ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
 
በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ዓመት ትምህርታችሁን በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች
ያጠናቀቃችሁ ምሩቃን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
 
ይህንን ምዕራፍ ያጠናቀቃችሁት በአስጨናቂው የኮቪድ19 ወረርሽኝ መካከል ቢሆንም፤፣ ትምሕርታችሁን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማጠናቀቅ ያሳያችሁት ቁርጠኝነት እና ጽናት የሚደነቅ ነው በማለት አስፍረዋል።
 
ለሁኔታው በሚስማማ መልኩ ራሳችሁን ማዘጋጀታችሁንም ያሳያል ሲሉ ለተመራቂዎች መልዕክት አስተላለፈዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለማችን የሚታዩት ፈጣን ለውጦች ለየሁኔታው በሚሆን መልኩ ራስን በማዘጋጀት፣ የትኛውንም ዓይነት መሰናክል ተቋቁመው በአሸናፊነት የሚወጡ ሰዎች መሆንን ይጠይቅብናል ብለዋል።
 
ቀጣዮቹን የሕይወታችሁን ምዕራፎች ስትጓዙ፣ ያካበታችሁት ዕውቀት እና ክህሎት ሀገራችሁን እና ዜጎቿን የሚያገለግል እንዲሆን ተስፋዬ እና እምነቴ ሲሉም ዶክተር ዐቢይ ገልፀዋል።
የሀገራችን የኢትዮጵያ ብልጽግና በትምህርታቸው አገናኝ ድልድዮችን ለመሥራት እና ገንቢ አሻራቸውን ለማሳረፍ በሚሹ ሴቶች እና ወንዶች ልጆቿ እጅ ላይ ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.