Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 555 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 8 ሺህ 490 የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 555 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
 
ሚኒስትሯ በ24 ሰዓታቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን ነው የገለፁት።
 
በአሁን ወቅት በፅኑ የታመሙ 66 ሰዎች እንደሚገኙ ያስታወቁት ሚኒስትሯ 181 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።
 
በዚህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 248 ሰዎች የደረሰ ሲሆን እነዚህም መካከል ቫይረሱ ያለባቸው 7 ሺህ 71 ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
 
ከበሽታው ያገገሙት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 5 ሺህ 966 እንደደረሰ ነው ሚኒስትሯ በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።
በኢትዮጵያ እስከአሁን በቫይረሱ ምክንያት 209 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
 
እንዲሁም ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ያደረገችው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ 372 ሺህ 812 የደረሰ ሲሆን ዕለታዊ የምርመራ እቅም ደግሞ ከ8 ሺህ በላይ ሆኗል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.