Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል መንግስት፣ ብልጽግና ፓርቲና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል መንግስት፣ የብልጽግና ፓርቲና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ላይም የፌደራል መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ነው፣ መንግስት የትግራይ ክልልንና ተወላጆችን እያገለለ ነው፣ ወዘተ የሚሉ የፕሮፖጋንዳ ትርክቶች ለፖለቲካ ፍጆታ ከመዋላቸው ባለፈ መሬት ላይ የሌሉ መሆናቸውን በመተማመን ላይ መደረሱን የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመልታል።

ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ልማት ላይ፣ የሀገር እድገት ላይ መዋእለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ የትግራይ ባለሀብቶች መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆምም ቃል እንደተገባላቸውም ተገልጿል።

ይህን ጉዳይ እየተከታተለ የሚያስፈፅም ተወካዮች መሰየማቸውም ነው የተገለፀው።

“አገር ሊፈርስ ነው ጓዝህን ጠቅልለህ ወደ ክልልህ ግባ” የሚለውን ውዥንብር ፕሮፖጋንዳ ሳይታለሉ ራሳቸውን አረጋግተው ሊሰሩ እንደሚገባም ተወያይቷል።

“ይህ በንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ናት፤ ሁላችንም ሰርተን የምንለወጥባት ሀገር እንጂ የምንሸማቐቅባት ሀገር አለመሆንዋንም ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል” ተብሏል በውይይት መድረኩ ላይ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.