Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን በዳርፉር ግዛት ተጨማሪ ወታደሮችን ልታሰፍር ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሱዳን በዳርፉር ግዛት ተጨማሪ ወታደሮችን እንደምታሰፍር ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ አስታወቁ፡፡

ከትናንት በስቲያ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 60 ንጹሃን ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ቀደም ባለው ቀን ደግሞ በተፈጸመ ተመሳሳይ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ መንግስት በአካባቢው የነዋሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ወታደሮችን እንደሚያሰፍር አስታውቋል፡፡

በተከታታይ ቀናት ለተፈፀሙት ጥቃቶች ሃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም መንግስት ግን በአከባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጥቃቱን ሳይፈፅሙት እንዳልቀሩ ገልጿል፡፡

በዳርፉር ከፈረንጆች 2003 ጀምሮ በተፈጠረ ግጭት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.