Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ሪፐብሊካኖች የ1 ትሪሊየን ዶላር የኮሮና ኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅድ ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የሪፐብሊካን ሴናተሮች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ከሚደርሰው የኢኮኖሚ ጫና ለማገገም የ1 ትሪሊየን ዶላር እቅድ ይፋ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ከእቅዱ ውስጥም ለአሜሪካ ትምህርት ቤቶች ማነቃቂያ 100 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ለበርካታ አሜሪካውያን በነፍስ ወከፍ የሚከፈል የ1 ሺህ 200 ዶላር ክፍያ መካተቱም ታውቋል።

ሪፐብሊካኖቹ በእቅዱ ዙሪያ የተመደበው ገንዘብ በቂ አይደለም በማለት ከሚከራከሩት ዴሞክራቶች ጋር መደራደር እንደሚጠበቅብቻውም ነው የተገለፀው።

አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ለማገገሚያ፣ ለኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እና ለግለሰቦች ከ2 ነጥብ 4 ትሪሊየን በላይ ወጪ ማድረጓ ተነግሯል።

አሁንም ቢሆን ግን በርካታ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ነው ኢኮኖሚስቶች የሚያሳስቡት።
ምንጭ፦ bbc.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.