Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ለክልልና ከተማ አስተዳደር የፓርቲው ጽ/ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ለክልልና ከተማ አስተዳደር የፓርቲው ፅህፈት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን አስረከበ፡፡

ዋና ጽህፈት ቤቱ 98 ሺህ ማስኮችንና 24 የሙቀት መለኪያዎችን ነው ለክልልና ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ያስረከበው፡፡

የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በርክክቡ ላይ እንደተናገሩት ÷ጥሩ እየተቆጣጠርን የነበረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመሃል ባጋጠሙ ችግሮችና እየታየ ባለው መዘናጋት ምክንያት ከፍ እያለ ነው፡፡

የኮሮና ቫይረስ በመከላከል ላይ አሁን እየታየ ያለውን መዘናጋት ለማስቀረት አመራሩ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ሃላፊው አሳስበዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ከአዲስ አበባ ውጭ እየታየ ያለው መዘናጋት የከፋ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

በመሆኑም የመከላከያ ቁሳቁሶችን በመጠቀም አመራሩ፣ የፓርቲው ጽህፈት ቤቶች ሰራተኞች እና ሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች ጥንቃቄ በማድረግ አርዓያ ይገባል በማለት አሳስበዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን የክረምት በጎ አድራጎት ስራ፣ የአረንጓዴ አሻራ ስራና የመህር ምርት ስራም ትኩረት እንዲሰጣቸው ጨምረው ማሳሰባቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.