Fana: At a Speed of Life!

የነብስ አድን ሰራተኞች የቤይሩቱን ፍንዳታ ተከትሎ የገቡበት የማይታወቅ ሰዎችን ለማግኘት ጥረት ላይ ናቸው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሊባኖስ የነብስ አድን ሰራተኞች በቤይሩት የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ የገቡበት የማይታወቅ ከ100 የሚበልጡ ሰዎችን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

እስካሁን በፍንዳታው የ100 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ 4 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የሟቾች ቁጥርም ሊጨመር እንደሚችል ተገምቷል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማይክል አውን ካቢኒያቸውን ለአስቸኳይ ስብሰባ የጠሩ ሲሆን፥ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅንም ሊታወጅ እንደሚችል ነው ያስታወቁት።

ፕሬዚዳንቱ ፍንዳታው በደረሰበት ቦታ ላይ 2 ሺህ 750 ቶን የሚመዝን አልሙኒየም ናይትሬት ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለስድስት ዓመታት ተከማችቶ ነበር ብለዋል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ሀገሪቱ ለሶስት ቀናት የብሄራዊ የሃዘን ቀን አውጃለች። ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዝደንቱ 66 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ፈንድ እንዲለቀቅ አዘዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.