Fana: At a Speed of Life!

በእንጅባራ ከተማ በ100 ሚሊየን ብር የተገነባው የቀረጢትና የምንጣፍ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መግስት በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በእንጅባራ ከተማ የተገነባው የቀረጢትና የምንጣፍ ፋብሪካ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

በ100 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፋብሪካ በአድማስ ሁለገብ የገበሬዎች ኀብረት ስራ ማኅበራት ዮኒየን አማካኝነት የተገነባ ነው ተብሏል፡፡

ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ከ700 በላይ ሠራተኞችን የሚይዝ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ200 በላይ ሰራተኞችን ይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ታውቋል።

ምርቱን ለኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ ለምርጥ ዘር አቅራቢዎች፣ ለግል ድርጅቶች፣ ለግለሰብ ነጋዴዎችና ለመሳሰሉት በጅምላ እንደሚያቀርብ ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኤጀንሲው አንዳስታወቀው ፋብሪካው ለተለያዩ ሰብሎች መያዣ ቀረጢት፣ የስኳር መያዣ ቀረጢት፣ የመሬት ማዳበሪያ ግብዓት መያዣ ቀረጢት፣ የከሰል መያዣ ቀረጢት፣ የግድግዳና የኮርኒስ አገልግሎት የሚሰጡ በልዩ ልዩ ቀለማት የተሠሩ እንዲሁም ለእምነት ተቋማት የሚውሉ የወለል ምንጣፎች አምርቶ ለገበያ እያቀረበ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.