Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብን በተመለከተ በዛሬው እለት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ስብሰባ ለአንድ ሳምንት ተራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በዛሬው እለት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ስብሰባ ሱዳን ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ለአንድ ሳምንት ተራዘመ፡፡

የኢፌዴሪ የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሃገራቱ ድርድሩን በመቀጠል የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በተካሄደ በሁለት ሳምንታት ውስጥ የመካከለኛና የመጨረሻ ሪፖርት ለህብረቱ ሊቀ መንበር እንዲያቀርቡ ይጠበቅ ነበር ብሏል፡፡

ይሁን እንጅ ግብጽ እና ሱዳን ባቀረቡት ማራዘሚያ ምክንያት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ድርድር ሳይካሄድ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ፅህፈት ቤት በፈረንጆቹ ሃምሌ 24 ቀን ባወጣው መግለጫ እና የሶስቱ ሃገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ በጋራ ሰነድ ላይ ለመስራት በደረሱት ደንብ መሰረት ኢትዮጵያ የበኩሏን የግድብ ሙሌት ደንብ አቅርባ እንደነበርም ነው ያስታወሰው፡፡

ቀጣዩ ድርድርም የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይጠበቃል ብሏል፡፡

በድርድር የሚደረስበት ስምምነት ብቸኛ አማራጭ በመሆኑም ኢትዮጵያ ለድርድሩ ውጤታማነት አበክራ ትሰራለችም ነው ያለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.