Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ ከእስር ቤት ለማምለጥ በተደረገ ሙከራ 10 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 5 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) በሶማሊያ ከእስር ቤት ለማምለጥ በተደረገ ሙከራ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ የሚገኘው ይህ እስር ቤት÷ የእድሜ ልክ ወይም የሞት ፍርድ የተፈረዱባቸው የታወቁ የአልሻባብ እስረኞች የሚገኙበት መሆኑ ተገልጿል።

እነዚህ እስረኞች ለማምለጥ ሙከራ ባደረጉበት ወቅት በተከፈተ ተኩስም የአስር ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።

የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ÷ ከሞቱት አስር ሰዎች ውስጥ ስድስቱ የአሸባሪው አልሸባብ አባላት ሲሆኑ ቀሪዎቹ አራቱ የጸጥታ ሰራተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከእስረኞቹ ውስጥ አንደኛው ከእስር ቤቱ ጠባቂ መኮንን መሳሪያ በመንጠቅና ተኩስ በመክፈት ከሌሎቹ የቡድን አባላቶቹ ጋር ሰብረው ለማምለጥ ሙከራ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ነገር ግን በቦታው ልዩ የፖሊስ ሀይል ተሰማርቶ ከእስር ቤት ለማምለጥ በተደረገው ሙከራ የተነሳውን ሁከት ማረጋጋቱ ተገልጿል።

በዚህ እስር ቤት በፈረንጆቹ 2017 እስረኞች ተመሳሳይ የማምለጥ ሙከራ ማድረጋቸውም ነው የተነገረው ።
ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.