Fana: At a Speed of Life!

ለ12ኛ ክፍል አይነ ስውራን ተማሪዎች እየተሰጠ ያለው የተስማሚ ቴክኖሎጂ ስልጠና በታሰበለት ደረጃ እየሄደ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 5 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ለ12ኛ ክፍል አይነ ስውራን ተማሪዎች እየተሰጠ ያለው የተስማሚ ቴክኖሎጂ ስልጠና በታሰበለት ደረጃ እየሄደ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ሁሉም አይነሰውራን ተማሪዎች በኦንላይን እንዲፈተኑ ለማድረግ በሙሉ አቅም እየተሰራ  ነው ብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሁሪያ ዓሊ ÷ተማሪዎቹ ፈተናውን በኦንላይን ለመፈተን የሚያስችላቸውን መሰረታዊ እውቀት እየያዙ መሆኑን ተናግረዋል።

ገና ስልጠናው ሳይጀመር ለፈተና ብቁ ሊሆኑ አይችሉም ብሎ መገመት ለተማሪዎቹ ዝቅ ያለ ግምት መስጠት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በተቻለ መጠን ለፈተና ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

እንደ አስፈላጊነቱ አጋዥ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎችም ለመመደብ እቅድ መያዙን አብራርተዋል።

የተስማሚ ቴክኖሎጂ ለአይነስውራን በኢትዮጵያ ዳይሬክተርና አሰልጣኝ  ዶክተር ታምሩ እውነቱ በበኩላቸው÷ ተማሪዎቹ እንደ የአካባቢያቸው ሁኔታ ከዚህ ቀደም የኮምፒውተር እውቀት ያላቸውና የሌላቸው በመሆናቸው ተመሳሳይ አቀባበል የላቸውም  ስለሆነም   ይህንን ታሳቢ በማድረግ ተማሪዎችን በመለየት ለፈተና ዝግጁ ለማድረግ ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል።

ተማሪዎቹ በበኩላቸው አብዛኞቻችን ከዚህ ቀደም የኮምፒውተር እውቀት ስለሌለን የስልጠናው ጊዜ ቢራዘም የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

ከመላ ሃገሪቱ የተውጣጡ 250 ዓይነ ስውራን ተማሪዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተስማሚ ቴክኖሎጂ ስልጠና እየወሰዱ ነው።

ስልጠናው ለፈተና ዝግጁ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ለሚኖራቸው የስራ ጊዜ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ እንደሚታሰብ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.