Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 584 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ20 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 11 ሺህ 881 የላብራቶሪ ምርመራ 584 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 24 ሺህ 175 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ20 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 440 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 285 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 696 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 520 ሺህ 891 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 24 ሺህ 175 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 37 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 190 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 10 ሺህ 696 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ420 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.