Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የጎዳና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች ህፃናና ወጣቶች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በጋራ በመተባበር በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የጎዳና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡

የጎዳና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራው መነሻውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማድረግ ለገሃር፣ ሜከሲኮ፣ ልደታ፣ ጦር ኃይሎች ተክለሃይማኖት አደባባዮች በመገኘት ተካሂዷል፡፡

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ ህዝቡ መዘናጋትን ወደጎን በመተው ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫው ቴዎድሮስ አደባባይ፣ አራት ኪሎ፣ ሲግናል፣ ሃያሁለት፣ ቦሌ ሩዋንዳ እና ቦሌሚካኤልንም አካቷል፡፡

ሚኒስትሯ ቫይረሱ እየተስፋፋ ያለበት ሰዓት በመሆኑና ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አስታውሰው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.