Fana: At a Speed of Life!

ከተለያዩ ተቋማት ከ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውሉ ድጋፎች ተደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ከ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውሉ ድጋፎችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አበረከቱ፡፡

በዚህም ባማኮን ኢንጂነሪንግ በቀን ለ200 ሰው አገልግሎት መስጠት የሚችል 100 የኦክሲጂን ኮንሰንትሬተር ማሽን፣ ዩ ኤስ ኤይድ – ዓለም አቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት ለ4 ሺህ 429 አባወራዎች የሚሆንና ለሶስት ወር የሚቆይ የ2 ሺህ ብር ድጋፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ቢዛ ራይድ 100 ሺህ ብር እና በርኪ ቴክኖሎጂ እና አሚኦ ኢንጂነሪንግ በጋራ 75 ሺህ ብር የሚገመት የፀረ ኢንፌክሽን ቻምበር ማሽን አበርክተዋል፡፡

ድጋፎቹን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ መረከባቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢንጅነር ታከለ ድጋፍ ላደረጉ አካላት በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪወች ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.